ለ157ቱ የአይሮፕላኑ ተሣፋሪዎች ዝክሩ የተደረገው በወደቀባት ከቢሾፍቱ 36 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሀማቁንጥሽሌ ቀበሌ ነው።
ከ2000 በላይ የቢሾፍቱ ከተማ ወጣቶች ተሰባስበው አደጋው የደረሰበት ሥፍራ ላይ በመገኘት ከተጎጂ ቤተሰቦች እና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ኀዘናቸውን ገልፀዋል።
ወጣቶቹ አደጋው ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ሲያዝኑ ለቆዩት የአካባቢው ነዋሪዎች የትምህርት ቁሣቁስ እርዳታ አድርገዋል፤ ከቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመተባበርም እዚያው ደም ለግሰዋል።
በመታሰቢያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የአደጋው ተጎጂ ቤተሰቦች በበኩላቸው አካባቢው ነዋሪዎች ትምህርት ቤት ወይም ጤና ጣቢያ እንደሚያሠሩ በተወካያቸው በኩል አስታውቀዋል።
እዚያው የተገኙ እምነቶችና የሃይማኖት አባቶች ለኀዘንተኛውና ለታደመው ሰው የማፅናኛ ቃል አሰምተዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ