በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቦይንግ 737 ማክስ ኤይት ጄት አደጋ ህይወታቸው ላለፈ መታሰቢያ


በቦይንግ 737 ማክስ ኤይት ጄት አደጋ ህይወታቸው ላለፈ መታሰቢያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:37 0:00

ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ለመጓዝ ከቦሌ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ በበረራ ቁጥር ኢቲ-302 እንደተነሣ በወደቀው ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት ጄት አደጋ ህይወታቸው ያለፈ መንገደኞች እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች የአርባ ቀን መታሰቢያ ዛሬ ተደርጎላቸዋል።

ለ157ቱ የአይሮፕላኑ ተሣፋሪዎች ዝክሩ የተደረገው በወደቀባት ከቢሾፍቱ 36 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሀማቁንጥሽሌ ቀበሌ ነው።

ከ2000 በላይ የቢሾፍቱ ከተማ ወጣቶች ተሰባስበው አደጋው የደረሰበት ሥፍራ ላይ በመገኘት ከተጎጂ ቤተሰቦች እና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ኀዘናቸውን ገልፀዋል።

ወጣቶቹ አደጋው ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ሲያዝኑ ለቆዩት የአካባቢው ነዋሪዎች የትምህርት ቁሣቁስ እርዳታ አድርገዋል፤ ከቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመተባበርም እዚያው ደም ለግሰዋል።

በመታሰቢያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የአደጋው ተጎጂ ቤተሰቦች በበኩላቸው አካባቢው ነዋሪዎች ትምህርት ቤት ወይም ጤና ጣቢያ እንደሚያሠሩ በተወካያቸው በኩል አስታውቀዋል።

እዚያው የተገኙ እምነቶችና የሃይማኖት አባቶች ለኀዘንተኛውና ለታደመው ሰው የማፅናኛ ቃል አሰምተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG