በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስክንድር ነጋ ተሸለመ


የእስክንድርን ሽልማት ባለቤቱ ሰርካለም ኒውዮርክ ላይ ተረከበች፡፡

በአሁኑ ወቅት በእሥር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ Pen America (ፔን አሜሪካ) ከተባለው የደራሲዎች ድርጅት የመፃፍ ነፃነት ሽልማት አግኝቷል።

የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ወይዘሮ ሰርካለም ፋሲል ትላንት ማታ በኒው ዮርክ ከተማ በተደረገው የድርጅቱ ዓመታዊ የእራት ግብዣ ሽልማቱን ተረክባለች።

እስክንድር በእሥር ላይ የሚገኘው አሸባሪነትን በመደገፍ ክስ ተመሥርቶበት ሲሆን ግጭትም ሆነ ሕገ-መንግሥታዊ ያልሆነ ለውጥ እንዲደረግ ቀስቅሶ እንደማያውቅ ገልጿል።

አሶሼትድ ፕሬስ የሚባለው የዜና አገልግሎት ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ባወጣችው ፀረ-ሽብር ሕግ መሠረት ወደ 200 የሚጠጉ ጋዜጠኞችን፣ ተቃዋሚዎችን፣ ፖለቲከኞችንና የተቃዋሚ ቡድኖች አባላትን አሥራለች ይላል።

ለጋዜጠኞች ደህንነት የሚሟገተው ኮሚቴ ደግሞ ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ ከኢትዮጵያ ጠፍተው የወጡት ጋዜጠኞች ቁጥር ከማንኛውም ሀገር የበዛ ነው ይላል።

የፔን አሜሪካ ማዕከል ፕሬዚዳንት ፒተር ጎድዊን እስክንድር ነጋን “ደፋርና እጅግ ከሚደነቁ ሰዎች አንዱ ነው” ሲሉ አሞግሰውታል። “እርሱ ራሱ ሲያሠምርበት የቆየው የሚነቅፉ ትችቶችን ወንጀል የሚያደርገው የኢትዮጵያ ፀረ-ሽብር ህግ ሰለባ ሆኗል” ሲሉም ተናግረዋል።

ዓለም አቀፉ የደራስያን ድርጅት ፔን በዓለምአቀፍ ደረጃ በሥራቸው ምክንያት ለታሠሩ ወይም አደጋ ላይ ለወደቁ ደራስያንና ጋዜጠኞች ይከራከራል።

ሰሎሞን ክፍሌ ከሰርካለም ፋሲል ጋር ቃለምልልስ አድርጓል፤ ያድምጡት

XS
SM
MD
LG