በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እነ እስክንድር ነጋ እንደገና ተያዙ

የምሥጋና ቀን በተመስገን ደሣለኝ ቤተሰቦች ቤት - መጋቢት 16/2010 ዓ.ም፤ ጃሞ-አዲስ አበባ

በቅርቡ ከእሥር የተፈቱትን እስክንድር ነጋን፣ ተመስገን ደሣለኝን፣ አንዱዓለም አራጌን በፍቃዱ ኃይሉን ጨምሮ 12 ሰዎች ዛሬ ምሽት ላይ በፖሊስ በቁጥጥር ሥር ዋሉ።

በቅርቡ ከእሥር የተፈቱትን እስክንድር ነጋን፣ ተመስገን ደሣለኝን፣ አንዱዓለም አራጌን በፍቃዱ ኃይሉን ጨምሮ 12 ሰዎች ዛሬ ምሽት ላይ በፖሊስ በቁጥጥር ሥር ዋሉ።

ፖሊስ ሰዎቹን ይዞ ያሠራቸው በተመስገን ደሣለኝ ቤተሰቦች ቤት ውስጥ የምሥጋና ቀን አዘጋጅተው ከእሥር በቅርቡ ለተፈቱ ሰዎች የደስታ መግለጫ ግብዣ ተደርጎ ሥነ-ሥርዓቱ ሊጠናቀቅ አካባቢ እንደነበር ተገልጿል።

የምሥጋና ቀን በተመስገን ደሣለኝ ቤተሰቦች ቤት - መጋቢት 16/2010 ዓ.ም፤ ጃሞ-አዲስ አበባ
የምሥጋና ቀን በተመስገን ደሣለኝ ቤተሰቦች ቤት - መጋቢት 16/2010 ዓ.ም፤ ጃሞ-አዲስ አበባ

የተያዙት ሰዎች ለፖሊስ ቃላቸውን እየሰጡ በነበረ ወቅት ካነጋገርናቸው መካከል ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሲያብራራ ፖሊስ እንደጥፋት የገለፀላቸው “ኮከብ የሌለው የኢትዮጵያ ባንዲራ ሰቅላችኋል” የሚል እንደነበረ አመልክቷል።

ከፖሊስ አባላቱ አንደኛው “ተመስገን ኃይለ-ቃል ተናግሮኛል፤ ሊደበድበኝ ተጋብዟል” ሲል መክሰሱን የጠቆመው እስክንድር የቀረበው አቤቱታ “ሃሰት ነው” ብሏል።

ይህ ዘገባ በአሜሪካ ድምፅ ለአየር እስከበቃበት ጊዜ ድረስ ሁሉም እሥረኞች እዚያው ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ-ከተማ ውስጥ በሚገኘው ጃሞ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ የነበሩ ሲሆን ፖሊስን ለማግኘት እያደረግን ያለነው ጥረት እንደተሣካ ተጨማሪ መረጃ እናቀርባለን።

ከእስክንድር ነጋና ከተመስገን ደሣለኝ ጋር የተደረገውን ቃለ-ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

እነ እስክንድር ነጋ እንደገና ተያዙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:17 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG