ትሬቮር ኖሃን እና ኬቨን ሀርትን የመሰሉ በምዕራቡ ዓለም የታወቁ የአደባባይ ኩመካ ባለሙያዎችን -“ስታንዳፕ ኮሜዲያንን” በማየት በመሰል የኪነ-ጥበብ መስክ ለመሰማራት መወሰኑን የሚናገረው ከያኒው፣ በጥቂት ወራት ፍርርቅ ሦስት የአደባባይ ኩመካ - ስራዎችን ለተመልካቾች አበርክቷል፡፡
በቅርቡ የወጣውን “ነግ በኔ” የተሰኘ ስራውን እንደመንደርደሪያ በመውሰድ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋር ቆይታ ያደረገው እሸቱ በአብዛኛው አድናቆትን፣ አልፎ አልፎ ደግሞ ወቀሳን ያስከተሉበትን ስራዎች- በሰዎች መካከል መነጋገር እና መስማማት እንዲጎለብት እንደ መሳሪያነት ለመጠቀም እየጣረ እንደሆነ አውስቷል፡፡
ከአሜሪካ ድምጹ ሀብታሙ ስዩም ጋር ያደረገው ቆይታ ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ