በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ድልድይን በሳቅ ለማነጽ የሚተጋው እሸቱ መለሰ (ኮሜዲያን)


ድልድይን በሳቅ ለማነጽ የሚተጋው እሸቱ መለሰ (ኮሜዲያን)
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:41 0:00

እሸቱ መለሰ ከጎሳ ፖለቲካ እስከ ማህበራዊ ጉዳዮች፣ከጾታዊ ጽንሰ ሀሳቦች እስከ ሰብአዊ መብት ሙግቶችን በሚዳስሱ አስቂኝ ስራዎቹ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትኩረትን ያገኘ ወጣት ከያኒ ነው፡፡ ትሬቮር ኖሃን እና ኬቨን ሀርትን የመሰሉ በምዕራቡ ዓለም የታወቁ የአደባባይ ኩመካ ባለሙያዎችን -“ስታንዳፕ ኮሜዲያንን” በማየት በመሰል የኪነ-ጥበብ መስክ ለመሰማራት መወሰኑን የሚናገረው ከያኒው፣ በጥቂት ወራት ፍርርቅ ሦስት የአደባባይ ኩመካ -የስታንድ አፕ ኮሜዲ ስራዎችን ለተመልካቾች አበርክቷል፡፡ በቅርቡ የወጣውን “ነግ በኔ” የተሰኘ ስራውን እንደመንደርደሪያ በመውሰድ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋር ቆይታ ያደረገው እሸቱ በአብዛኛው አድናቆት አልፎ አልፎ ደግሞ ወቀሳ ያስከተሉበትን ስራዎች በሰዎች መካከል መነጋገር እና መስማማት እንዲጎለብት በመሳሪያነት ለመጠቀም እየጣረ እንደሆነ አውስቷል፡፡ ከአሜሪካ ድምጹ ሀብታሙ ስዩም ጋር ያደረገው ቆይታ ያዳምጡ፡፡

እሸቱ መለሰ -ከጎሳ ፖለቲካ እስከ ማህበራዊ ጉዳዮች፣ከጾታዊ ጽንሰ- ሀሳቦች እስከ ሰብአዊ መብት ሙግቶች ፤ በሚዳስሱ አስቂኝ ስራዎቹ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትኩረትን ያገኘ ወጣት ከያኒ ነው፡፡
ትሬቮር ኖሃን እና ኬቨን ሀርትን የመሰሉ በምዕራቡ ዓለም የታወቁ የአደባባይ ኩመካ ባለሙያዎችን -“ስታንዳፕ ኮሜዲያንን” በማየት በመሰል የኪነ-ጥበብ መስክ ለመሰማራት መወሰኑን የሚናገረው ከያኒው፣ በጥቂት ወራት ፍርርቅ ሦስት የአደባባይ ኩመካ - ስራዎችን ለተመልካቾች አበርክቷል፡፡
በቅርቡ የወጣውን “ነግ በኔ” የተሰኘ ስራውን እንደመንደርደሪያ በመውሰድ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋር ቆይታ ያደረገው እሸቱ በአብዛኛው አድናቆት፣ አልፎ አልፎ ደግሞ ወቀሳ ያስከተሉበትን ስራዎች በሰዎች መካከል መነጋገር እና መስማማት እንዲጎለብት በመሳሪያነት ለመጠቀም እየጣረ እንደሆነ አውስቷል፡፡
ከአሜሪካ ድምጹ ሀብታሙ ስዩም ጋር ያደረገው ቆይታ ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG