ትናንት፤ ረቡዕ ስምንት ግጥሚያዎች ተካሂደዋል፡፡
ሚኔሶታ ፊላደልፊያን ሦስት ለባዶ፤ ፊኒክስ ፖርትላንድን ሦስት ለአንድ፤ ሂዩስተን ሳን ዲየጎን ሦስት ለሁለት፤ የሜሪላንዱ ሴንት ማይክል፤ ኢትዮ-ዳላስን ሁለት ለአንድ፤ ቦስተን ሳን ፍራንሲስኮን ሰባት ለአንድ፤ የሎስ አንጀለሱ ዳሎል አትላንታን አንድ ለባዶ፤ ዲሲ ስታር ሳን ሆዜን አንድ ለባዶ፤ ቨርጂንያ የሲአትል ባሮን ቡድን ሁለት ለባዶ አሸንፈዋል፡፡
ዲሲ ስታር፤ የሜሪላንዱ ቅዱስ ሚካኤልና የቨርጂንያው ላየን (አንበሣ) ቡድኖች ወደ ፍፃሜ ለመድረስም የተመቻቸ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ግጥሚያዎቹን እዚያው ተገኝቶ እየተከታተለ ያለው አዲሱ አበበ ዘግቧል፡፡
ነገ፤ ዓርብ የኢትዮጵያ ቀን የሚከበር ሲሆን ትናንት ምሽት ላይ ደግሞ የአካል ብቃት ባለሙያ የነበረውን ግርማ ቸሩን ለማክበር በበጎ ፍቃደኛች ደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል፡፡
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የክብር እንግዳ የሆነው አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ ፍቅሩ ኪዳኔ ስለግርማ ቸሩ እማኝነት ሰጥቷል፡፡
በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያዊያን የስፖርትና የባሕል ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ጌታቸው ተስፋዬም ከአዲሱ ጋር ባደረገው ቃለ-ምልልስ ስለ እንቅስቃሴው አጠቃላይ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ አሌክሳንድሪያ-ቨርጂንያ እየተካሄደ ያለውን የመላ ኢትዮጵያዊያን የስፖርት ማኅበር ቁጥር አንድ /በምኅፃር ኤሳ-ዋን ይባላል/ ዝግጅት በመቃወም ውድድሩ በሚካሄድበት ሜዳ መግቢያ ላይ የተሰለፉና ድምፃቸውን ያሰሙ ነበሩ፡፡
ከተቃዋሚዎቹ መካከል አንዷ ወ/ሮ ዮዲት ሺፈራው ከቪኦኤ ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዙትን ድምፆች ያዳምጡ፡፡