በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያውያን ዓመታዊ የመገናኛ ዐውደ ትርኢቱ(ፌስቲቫሉ) በዋይሊ ቴክሳስ ተጀመ


የኢትዮጵያውያን ዓመታዊ የመገናኛ ዐውደ ትርኢቱ(ፌስቲቫሉ) በዋይሊ ቴክሳስ ተጀመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:12 0:00

የሰሜን አሜሪካ ነዋሪ ትውልደ ኢትዮጵያውያን መገናኛ ሆኖ ለዓመታት የቆየው፣ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌዴሬሽን ዐውደ ትርኢት(ፌስቲቫል)፥ በዋይሊ ቴክሳስ፣ ትላንት እሑድ አመሻሹን በድምቀት ተጀምሯል።

ከ40 ዓመታት በፊት በዩስተን ቴክሳስ የተመሠረተው ፌዴሬሽኑ፣ የ40ኛ ዓመት ልዩ በዓሉን፥ ከመላ ዩናይትድ ስቴትስ የመጡ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን የእርስ በርስ ግንኙነት የሚሳድጉ መርሐ ግብሮችን፣ ለአንድ ሳምንት ለሚዘልቅ ጊዜ ያከናውናል፤ ተብሎ ይጠበቃል።

በዚኽ ፌስቲቫል ላይ፣ ከ30 በላይ የእግር ኳስ ቡድኖች መካከል ከሚደረገው ስፖርታዊ ፉክክር ጎን ለጎን፥ የመዝናኛ፣ የንግድ፣ የሰብአዊ ድጋፍ አገልግሎት እና የማኅበራዊ ግንዛቤ መርሐ ግብሮች ይካሔዳሉ።

ዋይሊ ቴክሳስ የሚገኘው ሀብታሙ ሥዩም ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG