በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌዴሬሽን 40ኛ ዓመቱን በዳላስ ቴክሳስ - ዋይሊ ስታዲዬም እያከበረ ይገኛል። ይኸው ዐውደ ትርኢት(ፌስቲቫል)፣ የኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዓመታዊ መገናኛ ሆኖ አራት ዐሥርት ዓመታትን ዘልቋል፡፡
ዘንድሮም፣ በባህል፣ በመዝናኛ፣ በንግድ፣ በበጎ አድራጎት፣ በፖለቲካ እና ማኅበራዊ አገልግሎት ውስጥ ተሳታፊ የኾኑ አካላት፣ ከመላ ዩናይትድ ስቴትስ ከመጡ በሺሕዎች ከሚገመቱ በትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋራ መስተጋብር ይፈጥሩበታል ተብሎ ይጠበቃል።