ሲያትል ዋሺንግተን —
በሰሜን ምዕራብ ዩናይትድ ስቴትሷ የዋሽንግተን ክፍለ ግዛት ዋና ከተማ ሲያትል በመካሄድ ላይ ያለው የሰሜን አሜሪካው የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባሕል ፌዴሬሽን ዓመታዊ ክብረ በዓል መክፈቻውን እሁድ ጨምሮ ስድስተኛ ቀኑን ይዟል።
ሰላሳ አራተኛውን ዓመታዊ ክብረ በዓል ለመከታተል ወደ ሥፍራው የተጓዘው አዲሱ አበበ በሰላሳ አንድ ቡድኖች መካከል ከሚካሄደው የእግር ኳስ ውድድር ትይዩ በሚከናወኑት ልዩ ልዩ የማሕበራዊና ፖለቲካ ነክ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ እንቅስቃሴዎችም ተመልክቷል።
በትላንትናው ምሽት የተከናወኑትንና ዛሬ የሚጠበቀውን ጨምሮ ማምሻው ላይ በስልክ አድርሶናል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ