በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢዜማ ጦርነት የተቀሰቀሰባቸውን አካባቢዎች መጎብኘቱን አስታወቀ


የሺዋስ አሰፋ
የሺዋስ አሰፋ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ /ኢዜማ/ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጦርነት በተቀሰቀሰባቸው የአማራና አፋር ሦስት ግምባሮች በመገኘት ጉዳት የደረሰባቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች በመጎብኘት ላይ መሆናቸው ተገለጸ።

ፓርቲው ኢትዮጵያዊያን እንደ አንድ በመቆም የተጋረጠባቸውን የህልውና ስጋት እንዲመክቱ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢዜማ ሊቀመንበር የሽዋስ አሰፋ ኢትዮጵያን ያድናል ሲሉ የገለጹትን ወታደራዊ ዘመቻ ሁሉም በመደገፍ አገራዊ ህልውናዋን እንዲያስቀጥል ታሰቦ የተዘጋጀ ጉብኝት ነው ብለዋል፡፡

የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚዎችም ወደአማራና አፋር የተለያዩ ግምባሮች መሰማራታቸው ታውቋል፡፡ ተፈናቃዮች የሚገኙበትን ሁኔታ አስከፊ ሲሉም ነው ያስረዱት ሊቀመንበሩ፡፡

እያንዳንዱን ዝርዝር የእርዳታ አሰጣጥና መሰል እውነታዎች የመረዳት እድል እንዳላገኙ የሚናገሩት ሊቀመንበሩ ሰብአዊ ጉዳቱን ግን በአንድ የተወሰነ አካል መመከት አይቻልም ባይ ናቸው፡፡ እንደ አገር የተጋረጠውን የህልውና አደጋ በጋራ እንመክት ሲሉ ነው ጥሪ ያስተላለፉት፡፡

ኢዜማ ጉዳት ለደረሰባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ቁሳዊና የገንዘብ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው ለአንዲት አገር እንደ አንድ መቆማቸው ያስመሰግናልም ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

ኢዜማ ጦርነት የተቀሰቀሰባቸውን አካባቢዎች መጎብኘቱን አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:54 0:00



XS
SM
MD
LG