በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአትላንታ - ጆርጂያ የኤርትራያዊያን ዓመታዊ ፌስቲቫል እየተካሄደ ነው


በሰሜን አሜሪካ የኤርትራዊያን የስፖርት ፌዴሬሽን /ኤሪስፋና/ ዓመታዊ ፌስቲቫል ዛሬ አምስተኛ ቀኑን ይዟል፡፡

ዕሁድ፤ ሰኔ 26/2008 ዓ.ም ጆርጅያ ግዛት ዋና ከተማ አትላንታ ላይ የተጀመረው በሰሜን አሜሪካ የኤርትራዊያን የስፖርትና የባሕል ፌስቲቫል አርባ አራት ቡድኖችን ይዞ ሲካሄድ ሰንብቷል፡፡

በግጥሚያዎቹ ላይ የተሠለፉት ከስምንት ዓመት እስከ 17 ዓመት በዕድሜ ክልል የተደራጁ ሃያ አራት የሕፃናትና የታዳጊዎች ቡድኖችና ዕድሜአቸው ከአሥራ ስምንት ዓመት በላይ የሆኑ ሃያ የአዋቂዎች ቡድኖች መሆናቸውን የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ደስታ አምባዬ ለቪኦኤ የትግርኛ ክፍል ባልደረባ ለተወልደ ወልደገብርኤል ነግረውታል፡፡

በጨዋታዎቹ ውስጥ የተካተቱት የእግር ኳስ ግጥሚያዎች፤ የሩጫ ውድድሮች በመቶ፤ ሁለት መቶ፤ አራት መቶ፣ ስምንት መቶና አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሜትሮች፤ እንዲሁም የቅርጫት ኳስና የቦውሊንግ ግጥሚያዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ካሉ የኤርትራዊያን ቡድኖች በተጨማሪ ከካናዳ የመጣ የቶሮንቶ ቡድንና ከእንግሊዝ የመጣ የለንደን ቡድንም እንደሚሣተፉ አቶ ደስታ አመልክተዋል፡፡

ከነገ በስተያ ቅዳሜ ከሚካሄደው የእግር ኳስ የዋንጫ ግጥሚያ፣ የዋንጫና የሜዳልያ ሽልማቶች በተጨማሪ የባሕል ዝግጅቶች እንደሚቀርቡ፤ የክብር እንግዳው የቀድሞ የቀይ ባህር ቡድን ተጨዋች የነበረው የማነ ካክሳይ /አቻዮ/ እና በዩናይትድ ስቴትስ የኤርትራ አምባሣደር ተወካይ፤ የማኅበረሰብ ጉዳዮች አቻሼው አቶ ዳዊት ኃይለ እንደሚገኙ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ደስታ አምባዬ ገልፀዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በአትላንታ - ጆርጂያ የኤርትራያዊያን ዓመታዊ ፌስቲቫል እየተካሄደ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:31 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


XS
SM
MD
LG