በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሶማሊያ መሪዎች - በባህርዳር


የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሶማሊያ መሪዎች ባህርዳር
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:13 0:00

የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሶማሊያ መሪዎች ባህርዳር

ጠ/ር አብይ አሕመድ፣ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ዐብዱላሂ ሞሐመድ አመሻሹን ባህርዳር ከተማ ገብተዋል፡፡

ጠ/ር አብይ አሕመድ፣ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እናየሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ዐብዱላሂ ሞሐመድ አመሻሹን ባህርዳር ከተማ ገብተዋል፡፡

መሪዎቹ ባህርዳር ከተማ ሲደርሱ የከተማዋ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አደርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ራሳቸው መኪና እያሽከረከሩም መሪዎቹን የባህርዳርን ከተማ አዘዋውረው አስጎብኝተዋቸዋል። መሪዎቹ ዛሬ ማለዳ ላይ በጎንደር ከተማ ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቀው ነው ባህር ዳር የገቡት።

ጠዋት ጎንደር ከተማ በነበራቸው ቆይታ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና በደምቢያ ወረዳ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል። ከሰዓት በኋላ የቡሬ የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ማቀነባበሪያ ፓርክም ጎብኝተዋል።

በባህር ዳር ከተማ በሚኖራቸው ቆይታም ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሕህመድ ጋር የሶስትዮሽ ውይይት ያደርጋሉ። መሪዎቹ የሚያደርጉት ውይይት ለአፋሪካ ቀንድ ሰላምና የኢኮኖሚ ትብብር የሚፈጥር ሲሆን በክልሉም የሕዝብ ለሕዝብ ትብብር ያጠናክራል ሲሉ አንድ የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን ገለፁ።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሶማሊያ መሪዎች - በባህርዳር
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:01 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG