አሥመራ - ኤርትራ —
ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚታየው አለመረጋጋት ምክንያቱ ‘የሕገ መንግሥቷ አንቀፅ 39 ነው’ ሲሉ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ አስታውቀዋል።
ሃገሪቱ ውስጥ ለሚስተዋለው “የጎሣና የብሄር” ሲሉ ለጠሯቸው ግጭቶችና አለመረጋጋት “ተጠያቂው ሕወሐት ነው” ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የቱርክን በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ወታደራዊ መስፋፋት፣ እንዲሁም በሱዳንና በኤርትራ መካከል ያሉ ግንኙነቶችን አንስተዋል።
የግብፅና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ወታደሮች ኤርትራ ገብተዋል ተብሎ የተሠራጨውንም ዘገባ ፕሬዚዳንቱ “ሃሰት ነው” ሲሉ አስተባብለዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ