አዲስ አበባ —
የኤርትራ መንግሥት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከሃያ ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ ሁኔታዎችን ለመርመር የመጣው የልዑካን ቡድን የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከፍተኛ አማካሪ የማነ ግብረአብና የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳላህ የሚገኙበት ነው፡፡
ዕለቱን ታላቅ ሲሉ የገለፁ በአቀባበሉ ሥነ ስርዓት ላይ የተገኙ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን የተጀመረው የሰላም ጥረት ውጤት እንደሚያስገኝ ተስፋቸውን አንፀባርቀዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ