በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የተከሰሰው ኤርትራዊ ጉዳይ


የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ቀንደኛው አለቃ ተብሎ የተከሰሰው እና በስም ስህተት እንጂ እኔ እይደለሁም ብሎ ሲከራከር የቆየው ኤርትራዊ ዕውነቱን መሆኑን የጣሊያን ፍርድ ቤት ወስኖለታት፣ ፍርድ ቤቱ ብይኑን የሰጠው ዛሬ ነው።

ከዓለም ዋና ዋና ህገ ወጥ የፍልሰተኛ አሸጋጋሪ መረቦች አንዱ የሆነ ቡድን ዋና አዛዥ ተብሎ የተከሰሰው መድህኔ ይህደጎ መርድ የተባለ ኤርትራዊ፤ ኤርትራ፣ ኢትዮጵያ፣ ሊቢያ፣ ሱዳን፣ የተባበሩት የአረብ ኤሚሬቶች አውሮፓን ጨምሮ ቅርንጫፎች እንዳሉት ተጠቅሷል።

እአአ በ2016 ሱዳን ውስጥ ተይዞ ለጣሊያን ተላልፎ የተሰጠው ግን እኔ መድሃኔ ተስፋ ማርያም በርሄ ነኝ ስራዬም አናጺ ነኝ ብሎ ሲሟገት ቆይቷል።

የሁለቱ ሰዎች መልክ አለመሳሰሉ ብቻ ሳይሆን የዘረመል (ዲኤንኤ) ምርመራ ማስረጃዎችም የታሰረውን መድሃኔን ሙግት ዕውነቱን ቢያሳይም፣ የጣሊያን አቃቤ ህጎች ግን አስራ አራት ዓመት እስራት እንዲፈረድበት ጠይቀዋል።

ዛሬ ዓርብ ነው ፓሌርሞ ላይ ያስቻለው ፍርድ ቤት ለመድሃኔ ተስፋ ማርያም በርሄ የፈረደለት።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG