በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤርትራ ካቶሊካዊት ቤተክርስታያን መግለጫ


በአጠቃላይ 30 የሚሆኑ በኤርትራ ካቶሊካዊት ቤተክርስታይን ሥር የሚሰሩ በመላ ኤርትራ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ የህክምና ማዕከላት በቅርቡ በኤርትራ መንግሥት በተዘጉበት ወቅት የካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ጳጳሳት ተቃውሞ አሰምተው ነበር። ነገር ግን ተገቢና ብቁ ምላሽ አላገኙም ይላል ባለፈው ረቡዕ የወጣ የኤርትራ ካቶሊካዊት ቤተክርስታያን መግለጫ።

መግለጫው አይያዞም በኤርትራ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ታጀዲን አብደልዐዚዝ ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩትን ጠቅሶ የተሳሳተ መረጃ ነው ይላል። አቶ ታጀዲን ዐብደል ዐዚዝ “የአስተዳደር ርክክብ ሥራ ነው የተካሄደው” የጤና አገልግሎቶችን የመዝጋት ዕርምጃ አልተወሰደም። የህክምና አገልግሎት ሰራተኞችንም ያስፈራራ የለም ማለታቸውን የኤርትራ የካቶሊክ ቤተክርስያን መግለጫ አውስቶ ምላሽ ሰጥቶበታል።

የተቋማቱን ባለቤት የሆነውን አካል ሳያሳውቁና ከሚመለከተው ባለሥልጣን ጋር ሳይመካከሩ በአንድ ወገን ትዕዛዝ ብቻ የንብረት ርክክብ ሊደረግ እንደማይችል ግልፅ ነው ይላል መግለጫው። በተረካቢውና በአስረካቢው መካከል ምንም ዓይነት የመረካከብ ሰነድ ሳይኖር ርክክብ የሚባል ነገር ሊኖር እንደማይችል መግለጫው አስገንዝቧል።

የኤርትራ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን መግለጫ በተጨማሪም የሥም ማጥፋት ዘመቻ እንደተከፈተበት ጠቁሟል። ኤድዋርዶ ካልካኞ የተባለ የቦንጆርኖ ኒውስ ጋዜጣኛ የኃፊነት ስሜትና የጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር በጎደለው መንፈስ በቤተክርስትያንዋ የህክምና ማዕከላት ያሉት ሰራተኞች ሙስና ውስጥ ተዘፍቀዋል የሚል ዘገጋ አቅርቧል። የኤርትራ መንግሥት ዕርምጃ የወሰደውም በዚህ ምክንያት እንደሆነ አስመስሎ አቅርቦታል ይላል መግለጫው።

ጋዜጠኛው ከአንድ ወገን ብቻ ያገኘውን ሳይሆን የሌላውን ወግን ትኩረትም ማካተት ነበረበት ሲል የኤርትራ ካቶሊካዊት ቤተክርስታያን መግለጫ ነቅፏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG