በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦሬገን ያሉት የኤርትራ አትሌቶች ተገኙ


ፎቶ ፋይል፦ እንደጠፉ ከተገለጹት መካከል አንዱ ኤርትራዊው አትሌት የማነ ተኽለሃዪም
ፎቶ ፋይል፦ እንደጠፉ ከተገለጹት መካከል አንዱ ኤርትራዊው አትሌት የማነ ተኽለሃዪም

ጠፍተዋል የተባሉት የኤርትራ አትሌቶች መገኘታቸውን የኦሬገን ዩኒቨርሲቲ ፖሊስ አስታወቀ።

አራቱ አትሌቶችና አሠልጣኛቸው መገኘታቸውንና የደረሰባቸው ጉዳት እንደሌለ የኤርትራ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማሳወቁን የዩኒቨርሲቲው ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለቪኦኤ በላኩት ኢሜል ገልፀዋል።

ቀድሞም ቢሆን አትሌቶቹ የደረሱበትን እንደማያውቅ ለፖሊስ ሪፖርት አድርጎ የነበረው ፌዴሬሽኑ እንደነበረ የፖሊሱ መግለጫ አክሎ አመልክቷል።

የኦሬገን ዩኒቨርሲቲ ፖሊስ በደረሰው ሪፖርት መሠረት ጠፉ የተባሉትን የኤርትራ አትሌቶች ከተፈላጊ ስዎች መዝገብ ማውጣቱንና መዝጋቱን አሳውቋል።

አትሌቶቹ ከቡድናቸው ጋር እንቅስቃሴአቸውን መቀጠላቸውን ፌዴሬሽኑ እንደነገረው ፖሊስ ገልጿል።

አትሌቶቹ የተሰወሩበትን ምክንያትና አሁን የት እንዳሉ ከቡድናቸው ለማወቅ ጥረት እያደረግን ነው፤ ተጨማሪ እንዳገኘን እናደርሳለን።

ዩጂን ኦሬገን ውስጥ ሰሞኑን በተካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የተሰለፉት አራት የኤርትራ አትሌቶችና አንድ አሠልጣኛቸው የገቡበት ጠፋ መባሉን ከኦሬገን አካባቢ ቴሌቪዥን ጣቢያ ኬቪኤኤል ያገኘነውን መረጃ ጠቅሰን ትናንት መዘገባችን ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG