በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤርትራ ማዕቀብ የተወሰነብኝ United States በኤርትራ ላይ ባላት ጠላታዊ አመለካከት ምክንያት ነው ትላለች


የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት ባለፈው ሰኞ በኤርትራ ላይ የቆየውን ማዕቀብ የሚያጠብቅ ውሳኔ መውሰዱ ይታወሳል። የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ታድያ ውሳኔው የተወሰደው United States በኤርትራ ላይ ባላት ጠላታዊ አመለካከት ምክንያት ነው የሚል መግለጫ አውጥቷል።

የኤርትራ የማስታወቅያ ሚኒስትር ዓሊ ዓብዱ ስለ መግለጫው ሲያብራሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሙሉ በሙሉ በ United States ቁጥጥር ስር ነው ያለው። ይህም ኤርትራ ብቻ ሳትሁን ሁሉም የሚለው ነው። ባለፈው የድርጅቱ 63 ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ወቅት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሙሉ ስልጣንና ቅርጽ ሁሉንም በሚያሳትፍ መንገድ እንዲዋቀር የተጠየቀውም ለዚህ ነው ብለዋል።

አቶ ዓሊ ዓብዱ አሜሪካ በኤርትራ ላይ አላት ስላሉት ጠላታዊ አመለካከት ሲናገሩም ለ 60 አመታት ያህል የዘለቀ ነው ብለዋል። "እአአ በ1950 ዎቹ አመታት ኤርትራ ነጻነት እንዳታገኝ ከልክላ ከኢትዮጵያ ጋር በፌደራላዊ አስተዳደር እንድትቆራኝ አድርጋለች። ነጻነት ከተገኘ በኋላም በሀርማን ኮሆን በኩል ነጻነትን ወደ ኋላ ለመመለስ ጥራለች። እአአ በ1993 አም የኤርትራ ህዝብ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና እንዳያገኝ የሚቻላትን ያህል እንቅፋት ሆናለች።"

"በኤርትራ በኩል ግን አሜሪካ የፈጸመችብንን በደሎች ባንረሳም ይቅር ብለን ከአሜሪካ ጋር ጥሩ ግንኙነት ለመመስረት ሞክረን ነበር። ኤርትራ ከጎረቤት ሀገሮች ጋር መልካም ግንኙነት መስርታ የኢኮኖሚና የንግድ ትብብርን አጠናክራ የኢጋድን ማለተም የምስራቅ አፍሪቃ በይነ መንግስታ የኢኮኖሚ ትብብር አላማን ወደ ልማት እንዲሰፋ አድርጋለች። United States ግን እንዲህ አይነቱን መልካም ተግባር አፈለገችም" ብለዋል ሚኒስትሩ።

XS
SM
MD
LG