በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ኤርትራ በሰብዓዊ መብት ረገጣ ተግባራዋ ቀጥላለች" የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት


“ኤርትራ በሰብዓዊ መብት ረገጣ ተግባራዋ ቀጥላለች” ሲሉ በሀገሪቱ ስላለው የሰብዓዊ መብት ሁኔታ የሚከታተሉት ልዩ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዘገባ አቅራቢ ገልፀዋል።

“ኤርትራ በሰብዓዊ መብት ረገጣ ተግባራዋ ቀጥላለች” ሲሉ በሀገሪቱ ስላለው የሰብዓዊ መብት ሁኔታ የሚከታተሉት ልዩ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዘገባ አቅራቢ ገልፀዋል።

የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ጠቢብ ለድርጅቱ የሰብዓዊ መብት ካውንስል ባቀረቡት አዲስ ዘገባ ኤርትራ በዜጎችዋ ላይ የሚፈፀመው ከባድ የሰብዓዊ መብት ረገጣ እንዲቆም የሚደረገውን ጥረት የማጓተት ተግባርዋን ማቆም አለባት ብለዋል።

ሼላ ቢ ኬታሩዝ የኤርትራ ህዝብ በዘፈቀደና በተገለለ እስራት፣ በገቡበት አለመታወቅና ከባርነት ኑሮ ጋር በሚመሳሰል ወታደራዊ አገልግሎት እየተሰቃየ ነው ብለዋል።

“እስካሁን ባለው ጊዜ የኤርትራ መንግሥት የምርመራ ኮሚሽኑ በስብዕና ላይ በሚፈፀም ወንጀል ደረጃ አድርጎ ያስቀመጠውን የሰብዓዊ መብት ረገጣን ለማቆ ያደረገው ጥረት እንደሌለ ስገልፅ ያሳዝነኛል” ሲሉ ልዩ ተወካይዋ አስገንዝበዋል።

ኬታሩዝ አያይዘውም ኤርትራ ከአንዳንድ የሰብዓዊ መብት አካላት ጋር የምታደርገው ግንኙነት የጨመረች ቢሆንም በመሬቱ ላይ የተለወጠ ነገር የለም ብለዋል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን 35ኛ ጉባዔ ለመገኘት የኤርትራ መልዕክተኞችን መርተው የተሳተፉት አምባሳደር ተስፋሚካኤል ገራህቱ ሸላ ይህን ዘገባ ያወጡት እንደልማቸው ወደ ኢትዮጵያ ሲመላለሱ ከከረሙ በኋላ ነው። ወይም በኤርትራ ላይ በጎ አመለካከት ከሌላቸው ወገኖች ጋር ከተገናኙ በኋላ ነው የሚል ምላሸ ሰጠዋል።

ኢትዮጵያ ራስዋ በኤርትራ ላይ በጎ ምኞት የሌላት ሃገር ከመሆንዋም በላይ በአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ የምትገኝ ሀገር ናት። ባለፈው ዓመት በተካሄደው ተቃውሞ ከ8መቶ በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ገድላ ከ26ሺሕ በላይ የሚሆኑትን አስራለች ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

“ኤርትራ በሰብዓዊ መብት ረገጣ ተግባራዋ ቀጥላለች” የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:55 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG