በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ተጥሎ የነበረውን ማዕቀብ አነሳ


በኤርትራ መንግሥትና ባለሥልጣናት ላይ የተነጣጠረው ማዕቀብ እንዲነሳ በብሪታንያ ተረቆ የቀረበውን ሃሳብ የፀጥታው ምክር ቤት በዛሬው ውሳኔው በሙሉ ድምፅ አጽድቆታል።

የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ተጥሎ የነበረውን ማዕቀብ አነሳ።

በኤርትራ መንግሥትና ባለሥልጣናት ላይ የተነጣጠረው ማዕቀብ እንዲነሳ በብሪታንያ ተረቆ የቀረበውን ሃሳብ የፀጥታው ምክር ቤት በዛሬው ውሳኔው በሙሉ ድምፅ አጽድቆታል።

የምክር ቤቱን ውሳኔ ተከትሎም አዲስ አበባ ላይ አስተያየት የሰጡት የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ “ማዕቀቡ ከአሁን በኋላ አያስፈልግም” ብለዋል።

የኤርትራ መንግሥት በበኩሉ “ቀድሞውንም መሆን ያልነበረበት” ያለውን ማዕቀብ መነሳት አስመልክቶ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ በማዕቀቡ ሳቢያ በሃገሪቱ እስካሁን ለደረሰው ጉዳት ካሳ እንደሚገባው አስታውቋል፡፡

ኤርትራ ለሶማሊያው እስላማዊ ጽንፈኛ ቡድን የመሳሪያ ድጋፍ ትሰጣለች በሚል የተባበሩት መንግሥታት ተቆጣጣሪዎች ያቀረቡትን ውንጀላ መሠረት በማድረግ ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት አሥመራ ላይ ተጥሎ የቆየው ማዕቀብ የጦር መሳሪያ ግዥን ጨምሮ የኤርትራን መንግሥትና የወታደራዊ ባለሥልጣናት ጉዞ፣ እንዲሁም የማንኛውንም ዓይነት ንብረት እንቅስቃሴ የሚገድብ ነበር።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG