አሥመራ —
በዚህ የኤርትራ ወጣቶች ብሔራዊ ቡድን 4 ለ 1 ያሸነፈበትን የወዳጅነት ግጥሚያ የኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣኖች፣ ኤርትራ የሚገኙ የሌሎች ሃገሮች አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች እንዲሁም የአሥመራ ከተማ የእግር ኳስ አፍቃሪዎች በአሥመራ ስታድየም ተገኝተው ተመልክተውታል።
በሌለ በኩል በስርድሎቭስኪ አውራጃ ምክትል አስተዳዳሪ ሚስተር ሰርጌ ቢዶንኮ የተመራው የሩሲያ መንግሥት የልዑካን ቡድን ዛሬ ረፋድ ላይ ከኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ዑስማን ሳልሕ ጋር ተገናኝተው በኢንቨስትመንና ንግድ፣ በጤና፣ በኢነርጂ፣ በውኃና የመድኃኒት አቅርቦት እንዲሁም በስፖርት መስች በትብብር ለመሥራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ