በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአስመራን ተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ ሰዎች እየታሰሩ መሆናቸው ተሰማ


ትናንት ማክሰኞ አስመራ ውስጥ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ፖሊሶች በወሰዱት የኃይል እርምጃ መበተኑ እና ተኩስ ተሰምቶ እንደነበር ዘገባዎች አመለከቱ።

ትናንት ማክሰኞ አስመራ ውስጥ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ፖሊሶች በወሰዱት የኃይል እርምጃ መበተኑ እና ተኩስ ተሰምቶ እንደነበር ዘገባዎች አመለከቱ።

ዩናይትድ ስቴትስ ኢምባሲ ስለተቃውሞ ሠልፉና ተኩሱ ሪፖርት እንደደረሰው ገልፆ አሜሪካውያን ጥንቃቄ ኣንዲያደርጉ አሳስቧል።

የተኩሱ ምንጭ ከየት እንደሆነ ግን አልታወቀም።

በፌስቡክና በትዊተር በተለቀቁና ዩቱብ ላይ በተለጠፉ በርካታ ቪዲዮዎች ላይ በርካታ ሰልፈኞች የመሃል አስመራን ጎዳናዎች ጥለው በሩጫ ሲሸሹ ይታያሉ የተኩስ ድምፅም ይሰማል።

ባልተረጋገጡ ዘገባዎች መሰረት የተቃውሞ ሰልፉ የጀመረው አብዛኞቹ ነዋሪዎች ሙስሊሞች በሆኑበት “አኸሪያ” የሚባለው የአስመራ ቀበሌ ነው።

አስመራ ውስጥ የሚገኘው “ዲያ አል እስላሚያ” የተባለው ትምህርት ቤት ሥርዓተ ትምህርቱን እንዲቀይር ከመንግሥት ትዕዛዝ ሰጥቶ ሃጂ ሙሳ መሃመድ ኑር የተባሉ አረጋዊ አባልን ጨምሮ የትምህርት ቤቱ ቦርድ እምቢ ማለቱ እና እና አንዳንዶቹ መታሰራቸውን የኤርትራን መንግሥትና ፖሊሲዎቹን የሚቃወመው

“አዋተ ዳት ካም” ድረ ገጽ ዘግቧል።

የትምህርት ቤቱን ተማሪዎቹንና ሌሎቹን የቦርዱን ዕርምጃ የሚደግፉትን የተቃውሞ ሰልፍ እንዲያደርጉ ያነሳሳቸው የሰዎቹ መታሰር መሆኑን አዋተ አክሎ አመልክቱዋል።

ከፓሪስ የኤርትራዊያን ጋዜጠኞች የራዲዮ ጣቢያ “ራዲዮ ኤረና” ባስተላለፈው ዘገባ ደግሞ የሀገሪቱ መንግሥት ትምህርት ቤቱ እንዲዘጋ ማዘዙን ተከትሎ ከአንድ መቶ በላይ ተማሪዎች ሰልፍ ወጥተው በአንድ ሰዓት ውስጥ ዱላና ጠመንጃ የታጠቁ የመንግሥት ኃይሎች በትነዋቸዋል።

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመሥቀል በትዊተራቸው የተቃውሞ ሰልፉን

“በአንድ ትምህርት ቤት የሆነና ካለምንም ጉዳት የተበተነ ለሰበር ዜናነት የማይመጥን” ሲሉ አጣጥለዋል።

ከአስመራ ከተማ ቪኦኤ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እና ሁኔታውን ከውጭ በቅርበት የሚከታተሉ “ከሰልፉ በተያያዘ የሞተም ይሁን የቆሰለ ሰው ስለመኖሩ የሰማነው የለም በርካታ ሰዎች እየታሰሩ መሆኑን ግን ሰምተናል” ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG