በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኤርትራ የታሰሩት አንጋፋ ፖለቲከኞችና ብዙ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ተጠየቀ


በኤርትራ 11 አንጋፋ ፖለቲከኞችና ብዙ ጋዜጠኞች ካለ ምንም ፍርድ ከታሰሩ አሰርተ-አመት ሆኗል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሶስት የቀድሞ የካቢኔ ሚኒስትሮች የሚገኙባቸው 11 አንጋፋ ፖሊቲከኞች የታሰሩት በሀገሪቱ ዲሞክራስያዊ ለውጥ እንዲደረግ በመጠየቃቸው እንደሆነ ገልጾ ለአስርተ-አመት ሙሉ ካለፍርድና ከማንኛውም ሰው ጋር በማይገናኙበት ሁኔታ ታስረው እንደሚገኙ ጡቁሟል። የኤርትራ መንግስት ካሰራቸው በኋላ በሀገሪቱ ጸጥታ ላይ ወንጀል ፈጽመዋል ብሏል።

በናይጀርያ የኤርትራ አምባሳደር የነበሩት አቶ አድሀኖም ገብረማርያም ግን“ፍርድ ቤት ቀርበህ ለመከራከር በማትችልበት፣ ነጻ ፕረስ በሌለበት፣ ሁለቱም ወገኖች ማስረጃዎች ይዘው ለመከራከር በማይችሉበት የኛ አይነት ስርአት መንግስት የፈለገውን ሊል ይችላል። ብቻውን የሚሮጥ የሚቀድመው የለም ብቻውን የሚከራከር ደግሞ የሚያሸንፈው የለም አሚል አባባል አለ” ሲሉ ገልጸውታል።

XS
SM
MD
LG