በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠ/ር አብይ አሕመድ ጎንደር ከተማ ገቡ


የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ዛሬ ጎንደር ከተማ ገቡ፤ የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት አቀባበል አደርገውላቸዋል ሲሉ መንግታዊ ዜና አውታሮች ዘገቡ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ዛሬ ጎንደር ከተማ ገቡ፤ የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት አቀባበል አደርገውላቸዋል ሲሉ መንግታዊ ዜና አውታሮች ዘገቡ።

የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ጉብኝት፣ በነገው ዕለት ጎንደር የሚገቡትን የኤርትራውን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ለመቀበል እንደሆነም ተገልጧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከጎንደር ከተማ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች ጋር መወያየታችውን በዚሁ መንግሥታዊ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

በዚሁ ውይይት፣ ምክትል ጠ/ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተገኘዋል።

ውይይቱም በክልሉ በተፈጠሩ ግጭቶች ዙሪያና የሀገር ሽማግሌዎች ችግሮቹን ለመፍታት እያደረጉ ባሉት ጥረት ላይ ያተኮር መሆኑም ተገልጧል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

ጠ/ር አብይ አሕመድ ጎንደር ከተማ ገቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:49 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG