ዋሽንግተን ዲሲ —
የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አራተኛው ፓትሪያርክ አቡነ ዲዮስቆሮስ ከረዥም ጊዜ ህመም በኋላ ዛሬ ማረፋቸው ታውቋል። ፓትሪያርኩ ከቅርብ ወራት ወዲህ በአገር ቤትና በውጭ ሀገር ሲታከሙ እንደቆዩ ተገልጿል።
የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሲኖዶስ በፓትሪያርኩ ማረፍ ጽኑ ሀዘን እንደሚሰማው ገልጿል።
የቀብር ስነ-ስርአት በመጪው ቅዳሜ መንደፈራ በሚገኘው የአቡነ አብራንዮስ ገዳም ላይ እንደሚፈጸም ታውቋል። የዜና ዘገባ አለን ከድምጽ ፋይሉ ያዳምጡ።