በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ እስራኤል ኤርትራውያን ስደተኞችን ወደ ሦስተኛ ሀገር እንዳትልክ ተቃወሙ

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ
የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በእስራኤል የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞችን ወደ ሌላ ሀገር ለማሽጋገር የቀረበው ሃሳብ ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል፡፡

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በእስራኤል የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞችን ወደ ሌላ ሀገር ለማሽጋገር የቀረበው ሃሳብ ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል፡፡

በቅርቡ ከኤርትራ ሬድዮና ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ በዓለም እየታየ ያለው የሰው ልጆች ፍልሰት፣ ሆን ተብሎ እየተደረገ ያለ የፖለቲካ ሴራ እንደሆነ ገልፀው፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ችግሩን እንዲመረምራ ያቀረቡት ሀሳብም መልስ እንዳላገኘ ገልፀዋል፡፡

በእስራኤል የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ፣ ከእስራኤል ጋር ያደረጉት የሀሳብ መለዋወጥም ስኬት አልባ ሆኗል ብለዋል፡፡

እስራኤል ኤርትራውያን ስደተኞችን ወደ ሦስተኛ ሀገር ለማዛወር ያደረገችውን ውሳኔ አጥብቀው ተቃውመዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ እስራኤል ኤርትራውያን ስደተኞችን ወደ ሦስተኛ ሀገር እንዳትልክ ተቃወሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:57 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG