በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሳዑዲ ዓረብያ

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከሳዑዲ ዓረብያ ንጉሥ ሳልማን ጋር
የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከሳዑዲ ዓረብያ ንጉሥ ሳልማን ጋር

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ዛሬ ሰኞ ከሳዑዲ ዓረብያ ንጉሥ ሳልማን ጋር ጅዳ ከተማ ተገናኝተው መወያይታቸውን የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስተር አስታወቀ።

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ዛሬ ሰኞ ከሳዑዲ ዓረብያ ንጉሥ ሳልማን ጋር ጅዳ ከተማ ተገናኝተው መወያይታቸውን የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስተር አስታወቀ።

በጅዳ ንጉሳው ቤተ መንግሥት ያካሄዱት ውይይት በሁለቱ ሃገሮች እና ሁለቱን ሃገሮች በሚመለክቱ ታላላቅ አካባቢያዊ ወይም ክልላዊ ጉዳዮች ያተኮረ እንደነበር ተገልፀዋል።

የሳዑዲ ንጉሥ ሳልማን ሃገራቸው ከኤርትራ ጋር ለአላት ወዳጅነት ታላቅ አክብሮት እንዳላት ገልፀው ግንኙነቷን ይበልጡን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን አመልክተዋል።

የሳውዲው ንጉስ በቅርቡ የኢትዮዽያ እና የኤርትራ መሪዎች በሀገሮቻቸው መካከል ሰላም ለመመስረት የወሰዱትን ብልኅነት እና ጀግንነት የተመላበት ርምጃ አድንቀዋል ብሏል መግለጫው።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ወደ ሳዑዲ የሄዱት ንጉሡ ባደረጉላቸው ግብዣ መሆኑንም አክሎ ገልፀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG