በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሥመራ በስተ ምሥራቅ የመሬት መንቀጥቀት ተከሰተ


የኤርትራ ካርታ
የኤርትራ ካርታ

በሪክተር መለኪያ 5.0 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ በአሥመራ በስተ ምሥራቅ 59 ኪሎሜትር ላይ ትናንት ማምሻውን መከሰቱን የአሜሪካ የሥነ ምድር ምርምር ተቋም አስታውቋል።

የመንቀጥቀጡ ማዕከል ከምጽዋ 39 ኪ.ሜ ላይ እንደነበርና ከመሬት ወለል 15 ኪ.ሜ. ጥልቀት ላይ እንደተነሳ ተቋሙ ገልጿል። መናወጡ ምናልባትም በኤርትራ በአጠቃላይ ሳይሰማ እንዳልቀረ ተነግሯል።

በመሬት መናውጡ የደረሰ ጉዳት ይኖር እንደሁ ገና አልታወቀም።

የኤርትራው መአድንና ኃይል ሚኒስቴር፤ በሪክተር መለኪያ 5.0 መጠን ያለው የመሬት መናወጥ ትናንት ከምሽቱ ለ9 ሰዓት 9 ደቂቃ ጉዳይ መከሰቱን አረጋግጧል ሲል የሀገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስቴር በለቀቀው መግለጫ አስታውቋል።

የመንቀጥቀጡ ማዕከል ከምጽዋ በስተደቡብ 41 ኪ.ሜ. ላይ ፣ እንዲሁም ጥልቀቱ 10 ኪ.ሜ. ላይ እንደነበር ሚኒስቴሩ ጨምሮ ገልጿል። ንዝረቱ በአሥመራ፣ ምጽዋ፣ መንደፈራ፣ አዲ ቀዪ፣ እና ሰነአፈ አካባቢው እንደተሰማ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

5.6 መጠን ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ ባለፍው ሐምሌ 25 እራፋይሌ በተባለ አካባቢ በሰሜን ቀይ ባህር ክልል መሰከቱን ሚኒስቴሩ አስታውሷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG