በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤርትራ የሰላም የባህል ቡድን ወደ አዲስ አበባ አቀና


የኤርትራ የሰላም የባህል ቡድን
የኤርትራ የሰላም የባህል ቡድን

የኤርትራ የሰላም የባህል ቡድን በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የሙዚቃ ዝግጅት ለማቅረብ ወደ አዲስ አበባ አቅንቷል።

የኤርትራ የሰላም የባህል ቡድኑ 62 አባላት ያሉት ሲሆን የተለያዩ ታላላቅ፣ አንጋፋና ታዋቂ እንዲሁም አዳዲስ ወጣት ዘፈኞችንና የስብሪት የባህል ቡድንን ያካተት ነው።

የሙዚቃ ዝግጅቱ ዋና ዓላማ በኤርትራና ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ሰላም ለማክበርና ሁለቱን ሀገራት በባህል በማስተሳሰር የሰላም ግንኙነቱን በይበልጥ ለማጠናክ ተብሎ የተዘጋጀ እንደሆነቡድኑን መርተው የሄዱት የኤርትራ የባህል ጉዳዮች ጽ/ቤት የሙዚቃ ኣላፍ አቶ እዮብ ሃብተኣብ ገልጸዋል።

የሰላም የባህል ቡድኑ ከየካቲት 16 እስከ የካቲት 21/2019 ባሉት ጊዚያት በባህርዳር፣ አዳማና ሃዋሳ እንዲሁም በአዲስ አበባ ሚለኒየም አዳራሽ ዘመናዊና ባህላዊ የሙዚቃ ዝግጅቶችን እንደሚያቀርብ ታውቋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

የኤርትራ የሰላም የባህል ቡድን ወደ አዲስ አበባ አቀና
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:33 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG