በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤርትራ በካናዳ ተቆጣች


ኤርትራ - ካናዳ
ኤርትራ - ካናዳ

ቶሮንቶ የሚገኙትን የኤርትራ ጠቅላይ ቆንሲል በአንድ ሣምንት ጊዜ ውሰጥ ከሃገር እንዲወጡ በማዘዝ የካናዳ መንግሥት የወሰደውን እርምጃ የኤርትራ መንግሥት በብርቱ እንደሚያወግዝ አስታውቋል፡፡
አቶ ሰመረ ገብረማርያም - በቶሮንቶ የኤርትራ ጠቅላይ ቆንሲል
አቶ ሰመረ ገብረማርያም - በቶሮንቶ የኤርትራ ጠቅላይ ቆንሲል

please wait

No media source currently available

0:00 0:02:06 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ቶሮንቶ የሚገኙትን የኤርትራ ጠቅላይ ቆንሲል በአንድ ሣምንት ጊዜ ውሰጥ ከሃገር እንዲወጡ በማዘዝ የካናዳ መንግሥት የወሰደውን እርምጃ የኤርትራ መንግሥት በብርቱ እንደሚያወግዝ አስታውቋል፡፡

የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ግንቦት 21 / 2005 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በቆንስላ ፅ/ቤቱ ሲሰጥ የቆየው አገልግሎት ሁሉ የቆንስላ ግንኙነቶችን በተመለከተ በቪየና ስምምነት በተደነገገው መሠረት የሚከናወኑና ዓለምአቀፍም ሆነ የካናዳን ሕጎች የሚጥስ አለመሆኑን አመልክቷል፡፡

“የቆንሲሉ እንዲወጡ መታዘዝ የካናዳ አስተዳደር በኤርትራ ላይ የከፈተው አግባብነት የሌለው የጥላቻ እና በዳያስፐራ በሚገኘው የኤርትራ ማኅበረሰብ ላይም የተፈፀመ የማጎሣቆል አድራጎት ነው” ብሏል፡፡

“ይህም በአንዲት አነስተኛ ነገር ግን ኩሩ ሃገር እና በሕዝቧ ላይ የተነጣጠረ የኃይል እርምጃ፣ የኤርትራ ማኅበረሰብ አባላትም ከመንግሥታቸው የሚፈልጉትን አገልግሎት እንዳያገኙ የተፈፀመ ነው” ብሏል የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ፡፡

ቆንሲሉ አቶ ሰመረ ገብረማርያምም አንዳችም ሕገወጥ አድራጎት አለመፈፀማቸውን ተናግረዋል፡፡

“የካናዳ መንግሥት የወሰደው እርምጃ እንደግለሰብ በእኔ ላይ ሣይሆን በኤርትራ ላይ ያለውን አቋም የሚያንፀባርቅ ነው፡፡ እኔ እንደ ቆንሲል ካናዳ ሆኜ ሕዝቤን የማገልገልና አስፈላጊውን መረጃ የመስጠት ሕጋዊ ኃላፊነት አለብኝ፡፡ እርምጃው ከቅን ማስረጃ ያልተነሣና በአሉባልታ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ እኔ ማድረግ የሚገባኝን ሥራ ስላሟላሁ የሚሰማኝ ምንም ነገር የለም፡፡” ብለዋል አቶ ሰመረ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል፡፡

ካናዳ ውስጥ ከሚኖሩ ኤርትራዊያን ላይ ታክስ ይሰበስባሉ በሚል በቶሮንቶ የኤርትራ ቆንሲል ሃገሪቱን በአንድ ሣምንት ለቅቀው እንዲወጡ በካናዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ቤይርድ መታዘዛቸው ይታወሣል፡፡

ሰመረ ገብረማርያም በምሥራቅ አሜሪካ የጊዜ አቆጣጠር ግንቦት 28 / 2005 ዓ.ም ዕኩለ ቀን ባለው ጊዜ ከሃገራቸው እንዲወጡ የጠየቋቸው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጆን ቤይርድ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

ቤይርድ በመግለጫቸው ላይ “ኤርትራ የተጣሉባትን ዓለምአቀፍ ማዕቀቦች እና የካናዳንም ሕግ እንድታከብር ካናዳ ኤርትራን በተደጋጋሚ አሳስባለች፤ የዛሬው እርምጃም ስለራሱ የሚናገር ነው” ብለዋል፡፡

በቶሮንቶ የኤርትራው ቆንሲል አቶ ሰመረ ከሃገር እንዲወጡ የተወሰነበትን ዝርዝር ምክንያት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቤይርድ ቢሮ ባይገልፅም እርምጃው የተከተለው ሲቢኤስ የሚባለው የዜና አውታርና ሌሎችም የካናዳ መገናኛ ብዙኃን ቆንስላው ስለሚሠራቸው ሥራዎች ዘገባዎችን ባወጡ ሰሞን መሆኑ ታውቋል፡፡

የካናዳ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን - ሲቢኤስ ባወጣው ዘገባው ኤርትራዊያኑ በሁለተኛ ታክስነት የአምስት መቶ ዶላር ክፍያ ለቆንስላው ፅሕፈት ቤት እንዲፈፅሙ የሚደረጉ መሆኑንና ይህም የኢትዮጵያን ወረራ ለመመከት የሚሰጥ የብሄራዊ መከላከያ እርዳታ ተደርጎ እንደሚወሰድ አመልክቷል፡፡

ዘገባውን ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG