«ይህ ማለት ግን» ይላል ካዲሳባ የደረሰን የፒተር ሃይንላየን ዘገባ «የሕብረቱ ዋና መዲና መቀመጫ ከሆነችው ጎረቤቷ ኢትዮጵያ ጋር ያላት ቅራኔ ላልቷል ማለት አይደለም።»
በአፍሪካ ሕብረት የኤርትራ አምባሣደር ግርማ አስመሮም ተስፋዬ የሹመት ደብዳቤአቸውን ከሁለት ቀናት በፊት ለኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ዣን ፒንግ አስረክበዋል፡፡
ኤርትራ ከአሥር ዓመታት በኋላ አሁን ሃምሣ ሦስት አባላት ወደሉት የአፍሪካ ኅብረት መቀላቀሏ አስደሣች መሆኑን ሊቀመንበሩ ፒንግ ገልጠዋል፡፡ የሊቀመንበርነቱን ሥልጣን ከሦስት ዓመታት በፊት የተረከቡት ፒንግ ከሥራዎቻቸው መካከል የኤርትራ ዳግም መቀላቀል ከፍተኛው ስኬታቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ኤርትራ ከኅብረቱ አምባሣደሯን ያስወጣችው በአውሮፓዊያኑ የዘመን አቆጣጠር ከ1998 እስከ 2000 የነበረውን የድንበር ውዝግብ ከፍፃሜ ያደረሰው የሠላም ስምምነት ተግባራዊ እንዳይሆን "ኢትዮጵያ ጥሣ ሳለ ኅብረቱ ድርጊቱን ያለማውገዝ ድክመት አሣይቷል" የሚል ቅሬታ አሰምታ ነበር፡፡
የአፍሪካ ኅብረት ያንን ስምምነት ካደራደሩ አካላት ዋነኛው እንደነበር አይዘነጋም፡፡
ዝርዝሩን ከዘገባው ያድምጡ፡፡