በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤርትራ ውስጥ መነኮሳት ታሰሩ


Pastor Halefom Charlotte
Pastor Halefom Charlotte

ኤርትራ ውስጥ ባለፈው ሳምንት አምስት የደብረ ቢዜን ገዳም መነኮሳት በፖሊስ ተይዘው መታሰራቸው እና እስካሁንም ጊንዳይ ከተማ እንደታሰሩ መሆናቸው ተገለጠ። ከዩናይትድ ስቴትስ እና ከእስራኤል የአብያተ ክርስቲያን ምንጮች ለቪኦኤ ገልፀዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ሰሜን ካሮላይና ሻርለት ከተማ የሚገኘው የኤርትራ ኦርቶዶክሳዊት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ቄስ ሃለፎም አንደማርያም “የቀድሞ መምህራኔ” ሲሉ የጠሩዋቸው መነኮሳቱ የተያዙት አዲሱን የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተክስራቲያን አስተዳደርና የሀገሪቱ መንግሥት በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን በመቃወማቸው ነው ሲሉ ለባልደረባችን ለተወልደ ወልደገብርኤል ገልፀዋል።’

ከኤርትራ መንግሥት ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

በእስር ላይ ያሉት መነኮሳት አባ ክብረአብ ተኪኤ፣ አባ ማርቆስ ገብረኪዳን፣ አባ ኪዳነ ማርያም ተከስተ፣ አባ ገረትንሳኤ ዘ/ሚካኤል እና አባ ገብረትንሳዔ ተወልደ መድህን እንደሚባሉ ምንጮቹ ጠቁመዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG