ዋሺንግተን ዲሲ —
የቱርክ ፕሬዚዳንት ረጂብ ታይፕ ኤርዶዋን ዛሬ የዩናይትድ ስቴትስ የኤሌክትሮኒክ ዕቃዎችን መግዛት ለማቆም ዝተዋል። አሜሪካ በቱርክ ላይ ዒላማ የለየ የኢኮኖሚ ጦርነት እያካሄደች ነው በማለት ነው ዛቻውን ያሰሙት።
በሁለቱ ሀገሮች መከከል የተከሰተው የዲፕሎማሲ ፀብ ቱርክ ላይ የኢኮኖሚ ቀውስ አስከትሎ “ሊራ” የተባለው ገንዘቧ ዋጋ ቁልቁል እንዲወርድ አድርጓል። የሀገሪቱን ገንዘብ ለማጠንከር ሲባል ሰዎች ያላቸውን ዶላር በሊራ እንዲቀይሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ