በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰበር ­ዜና:- ዶ/ር አብይ አህመድ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ


ዛሬ ስብሰባውን ያጠናቀቀው የኢህአዴግ ምክር ቤት የኦህዴዱን ዶ/ር አብይ አህመድን ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡

ዛሬ ስብሰባውን ያጠናቀቀው የኢህአዴግ ምክር ቤት የኦህዴዱን ዶ/ር አብይ አህመድን ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡

ዶ/ር አብይ ቀጣዩ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡

ምክር ቤቱ የግንባሩ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው የቆዩት አቶ ደመቀ መኮንን በያዙት ኃላፊነት እንዲቀጥሉ ወስኗል፡፡

ከአምስት ዓመታት በላይ ለሆነ ጊዜ የግንባሩ ሊቀመንበርና የሀገሪቱ ጠ/ሚ ሆነው የቆዩትን የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን የሥልጣን መልቀቂያ ጥያቄም ተቀብሏል፡፡

ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ በስብሰባ ላይ የቆየው የኢህአዴግ ምክር ቤት፣ ስብሰባውን ያጠናቀቀው ዛሬ ረቡዕ ወደ እኩለ ሌሊት በተጠጋ ሰዓት ነው፡፡

ከዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በሊቀመንበርነት የተወዳደሩት የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ አቶ ሽፈራው ሽጉጤና የህወሃቱ ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል መሆናቸውን የኢህአዴግ ምንጮች ማምሻውን ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG