አዲስ አበባ —
ከገዥው ፓርቲና ከሀገር አቀፍ ፓርቲዎች ለድርድር የቀረቡ አጀንዳዎችን የሚያጠናቅረው የአጀንዳ የአደራጅና የሚዲያና የኮሙዩኒኬሽን ኮሚቴ ዛሬ ሥራውን ጀምሯል፡፡ ድርድሩ ሊጀመር የሚችለው ፓርቲዎቹ በተደራጁት አጀንዳዎች ላይ ከሥምምነት ከደረሱ በኋላ መሆኑን ተገልጿል፡፡
በተቃዋሚ ፓርቲዎች ከቀረቡት አጀንዳዎች መካከል የፖለቲካና የሕሊና እሥረኞች መፈታትና የፀረ ሽብር ሕጉ መሻሻል እንደሚገኝበት የመኢአድ ምክትል ፕሬዚዳንት ለአሜሪካ ድምፅ አስረድተዋል፡፡
በገዥው ኢህአዴግና በሀገር አቀፍ ፓርቲዎች መካከል የሚደረገው ድርድር በሚመራበት ሠነድ ላይ ከሥምምነት በመደረሱ አሁን ትኩረቱ በአጀንዳዋች ላይ ሆኗል፡፡ ኢህአዴግና ተቃዋሚዎቹ በምን በምን ጉዳዮች ላይ እንደሚደራደሩ ገና አልተወሠነም፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ