አዲስ አበባ —
የደቡብ ሱዳን ገዥ ፓርቲ - የሱዳን ሕዝብ አርነት ንቅናቄ - ኤስፒኤልኤም ውስጣዊ ችግር ከተፈታ የሃገሪቱ ችግርም ሊፈታ ይችላል ሲሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢህአዴግ ሊቀመንበር ኃይለማርያም ደሣለኝ ተናግረዋል፡፡
ፓርቲው ራሱን ለሚገመግምበትና ለሚያይበት ቀጣይ ስብሰባ መንገድ የሚጠርግ ውይይት አዲስ አበባ ላይ ተከፍቷል፡፡
ውይይቱን የሚያስተባብሩትና የሚመሩት የኢትየጵያው ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግና የደቡብ አፍሪካው ገዥ ፓርቲ የአፍሪካ ብሔራዊ ምክር ቤት - ኤኤንሲ ሲሆኑ በኢትየጵያ በኩል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ አቶ በረከት ስምዖን በዚሁ ኃላፊነት ተሰይመዋል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡