ዋሺንግተን ዲሲ —
ከኢትዮጵያው ገዢ ፓርቲ ኢህአዴግ ጋር ለመደራደር ፈቃደኛ የሆኑ የተቃውሞ ድርጅቶች እየተደራደሩ መሆናቸው ያታወቃል።
የድርድሩ ሂደት በአሁኑ ወቅት ምን ላይ እንደደረሰ እንዲያብራሩልን የመኢአድ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አበበንና የኢደፓ ሊቀመንበር ዶክተር ጫኔ ከበደን ጋብዘናል።
የድርድሩ ዋና ዓላማ ችግሮችን በውይይት ለመፍታት የሚያስችል አሰራር እንዲፈጠር እንዲሁም ብሔራዊ ስሜት ከሌለ አንድነት ሊኖር ስለማይችል ብሔራዊ ስሜት እንዲሰርፅ ለማድረግ መሆኑን ገልፀዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ