በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አቡነ ኤርሚያስ በጦርነቱ ለተጎዱ ጠንካራ እገዛ እንዲደረግ ጠየቁ


አቡነ ኤርሚያስ በጦርነቱ ለተጎዱ ጠንካራ እገዛ እንዲደረግ ጠየቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:58 0:00

አቡነ ኤርሚያስ በጦርነቱ ለተጎዱ ጠንካራ እገዛ እንዲደረግ ጠየቁ

በአማራ ክልል ምስራቃዊ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎችን በማጽናናት፣ የመተባባር መንፈስን በመፍጠርና የከፋ ሰብዓዊ ጉዳት እንዳይደርስ በማድረግ አስተዋጾ አበርክተዋል የተባሉ የኃይማኖት አባቶች በደሴ ከተማ ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።

የሰሜንና ደቡብ ወሎ እንዲሁም የኦሮሞ ብሔረሰብ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ኤርሚያስ ጦርነቱ ያስከተለው ሥነ ልቦናዊና ቁሳዊ ጠባሳ የከፋ መሆኑን አውስተው የወደሙ ተቋማትን መልሶ በማቋቋምና የተቸገሩትን በማገዝ ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጠይቀዋል፡፡

እምነትንና አካባቢን ሳይለዩ ሁሉንም በሰብአዊነት አገልግለዋል የተባሉ አራት ሊቃነ ጳጳሳት ትናንት በደሴ ከተማ በተዘጋጀ ልዩ መርኃ ግብር እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG