የበለስ ተክል በኢትዮጵያ ሰሜን አካባቢዎች በስፋትና በሌሎችም የሃገሪቱ ክፍሎች የሚታወቅ ተክል ነው፤ በአንዳንዱ አካባቢ ለጥቅም ይውላል፣ በሌላው ደግሞ ብዙም አይሰበሰብም እንጂ፡፡
በተለይ ድርቅ በሚበረታበትና የምግብ እጥረት በሚያጋጥምበት ጊዜ ነፍስ አድን ተክል በመሆኑ ይታወቃል፡፡
በለስ ከዚያ ልማዳዊ አጠቃቀም ወጥቶ የኢንዱስትሪ ውጤትን፣ የተለያዩ የምግብና ሌላም ሸቀጥ ሆኖ ለሃገር ውስጥና ለውጭም ገበያ የሚቀርብበትን ሥራ ለመፍጠር ለረጅም ዓመታት በምርምርና ልማት ተግባር ላይ የቆዩት አቶ ተስፋዬ ዓለምሰገድ በተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት ፕሮግራም ይናገራሉ፡፡
ዝግጅቱ በተጨማሪም፡-
አዲስ አረም በአፋር ችግርና ሥጋት ፈጥሯል፤
በታላላቅ ሐይቆች ፀረ-ሕይወት ቅመሞች፤
ማዕከላዊ ቻይና በድርቅ ተመታ፤
የኢራኑ ግዙፉ ኦሩሚዬ ሐይቅ የጨው ምድር እየሆነ ነው፤ የሚሉ ዜናዎች ተካትተዋል፤ ያዳምጡት፡፡