በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደመናን መረዳት


የዓለም ሚቲኦሮሎጂ ቀን መጋቢት 14 “ደመናን መረዳት” በሚል መሪ ቃል በመላው ዓለም ታስቦ ውሏል፡፡

የዓለም ሚቲኦሮሎጂ ቀን መጋቢት 14 “ደመናን መረዳት” በሚል መሪ ቃል በመላው ዓለም ታስቦ ውሏል፡፡

ዕለቱ በይፋ የሚከበረው ስድሣ ሰባት ዓመት የሆነው የዓለም የሚቲኦሮሎጂ ድርጅት የተመሠረተበትን ዕለት ለማሰብ ሲሆን የዘንድሮው ሃምሣ ስድስተኛው ክብረ በዓል ነው፡፡

ዕለቱ በኢትዮጵያም በብሔራዊ ደረጃ ሐዋሳ ከተማ ላይ መከበሩን ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ማብራሪያ የገለፁት የዓለም ሚቲኦሮሎጂ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዱላ ሻንቆ ሰሞኑን እየታየ ያለው ደረቅ አየር ኢትዮጵያ ውስጥ ውርጭ ማስከተሉን አመልክተዋል፡፡

ይሁን እንጂ “ከሕንድ ውቅያኖስ ይነፍሳል” የተባለው ንፋስ ርጥብ አየር በምሥራቅ አፍሪካ ላይ እንደሚያስከትልና ዝናብ ያመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ አቶ ዱላ አመልክተዋል፡፡

እጅግ አስከፊ በተባለ ድርቅ ሳቢያ ወደ ሃያ ሚሊየን የሚሆን ሰው በዚህ ዓመት አፍሪካ ውስጥና በአረቢያ ልሣነ ምድር ደቡብ አካባቢዎች ላይ ለበረታ ረሃብ እንደሚጋለጥ የተለያዩ ዓለምአቀፍ ተቋማት እያስጠነቀቁ ነው፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ደመናን መረዳት
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:50 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG