በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"መነጋገር፤ መነጋገር፤ መነጋገር" - የኢትዮጵያዊያን ጉባዔ በሲያትል


"ብሔራዊ አንድነቷ የተጠበቀ፣ ሰላም የሠፈነባትትና የበለፀገች አንዲት ኢትዮጵያን ማየት!" ባለፈው ቅዳሜና ዕሁድ፤ ግንቦት 19 እና ግንቦት 20 / 2009 ዓ.ም የምዕራብ ዩናይትድ ስቴትሷ ዋሺንግተን ግዛት ውስጥ በሴአትል ከተማ ተጠርቶ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ጉባዔ ተሣታፊዎች ራዕይ ነው፡፡

"ብሔራዊ አንድነቷ የተጠበቀ፣ ሰላም የሠፈነባትትና የበለፀገች አንዲት ኢትዮጵያን ማየት!" ባለፈው ቅዳሜና ዕሁድ፤ ግንቦት 19 እና ግንቦት 20 / 2009 ዓ.ም የምዕራብ ዩናይትድ ስቴትሷ ዋሺንግተን ግዛት ውስጥ በሴአትል ከተማ ተጠርቶ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ጉባዔ ተሣታፊዎች ራዕይ ነው፡፡

ጉባዔው ለሁለት ቀናት ተነጋግሮ ሥራውን ሲያጠናቅቅ ባወጣው የአቋም መግለጫ ይህ በዓይነቱ የመጀመሪያ ነው የተባለ የንግግር መድረክ በቀጣይነት በየዓመቱ በተለያዩ ከተሞች እንዲዘጋጅ ወስኗል፡፡

ተሣታፊዎቹ ባወጡት ባለአሥር ነጥብ የአቋም መግለጫ ላይ የአጭርና የረጅም ጊዜ ትልማቸውንም አስፍረዋል፡፡ «ሃገራችን በሽግግር ሂደት አልፋ በሕዝብ ነፃ ምርጫ ላይ ወደ ተመሠረተ ዴሞክራሲያዊ መንግሥታዊ ሥርዓት እንድትሸጋገር ማስቻል፤ ለሁላችንም የምትመች ሰብዓዊ መብቶች የሚከበሩባት፣ እውነተኛ እኩልነት፣ ፍትኅና የሕግ የበላይነት የተረጋገጡባትና ዘላቂ ሰላም የሠፈነባት ዴሞክራሲያዊት ሃገር እንድትኖረን ማድረግ» ይላል ሠነዱ፡፡

ጉባዔው ሲዘጋጅ ዋነኛ ዓላማው ያለማቋረጥ መነጋገር የሚቻልበትን መድረክ ማሰናዳት፤ ንግግር እንዳይቋረጥ ማድረግ ነበር፡፡

የሲያትሉ ጉባዔ ቀድሞ ሳይነገናኙ የኖሩ፣ እንዲያውም በተለያዩ ወቅቶች በመረረ ፀብ ይፈላለጉ የነበሩ የፖለቲካ ሰዎችን ማገናኘት የቻለና የተሣካ እንደነበር የአዘጋጁ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ጉባዔ በሲያትል ሊቀመንበር ዶ/ር አሸናፊ ጎሣዬ ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡

በጉባዔው ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው በንግግር የከፈቱት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ናቸው፡፡

ለተጨማሪ በጉባዔው ላይ የተጠናቀረውን ዘገባና ከሊቀመንበሩ ከዶ/ር አሸናፊ ጎሣዬ ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ የያዙ የድምፅ ፋይሎችን ያዳምጡ፡፡

የኢትዮጵያዊያን ጉባዔ በሲያትል (ዘገባ)
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:09 0:00
የኢትዮጵያዊያን ጉባዔ በሲያትል (ከዶ/ር አሸናፊ ጎሣዬ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ)
please wait

No media source currently available

0:00 0:19:23 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG