እንሥራ የሸክላ ሥራ ማኅበር ከ400 በላይ ሴቶች የሸክላ ምርቶች የሚያመርቱበት ማዕከል ነው፡፡
በማዕከሉ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የሸክላ ውጤቶች ይመረታሉ፡፡ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ እንዲኾኑ ተደርገው የተዘጋጁት የሸክላ ምርቶች ከአፈር ዝግጅት ጀምሮ እስከመጨረሻው ውጤት በእጅ ተሠርተው ለገበያ የሚቀርቡ ናቸው፡፡
ለቡና ማፍያ የሚያገለግለው ጀበና ለምግብ ማብሰያ እና መመገቢያ የሚያገለግሉት ድስት፣ ምጣድና የሸክላ ሰሃንን የመሳሰሉትና፣ እንዲሁም ለአበባ መትከያ እና ለጌጣጌጥነት የሚውሉ የሸክላ ውጤቶች የሚመረቱበት ስፍራ ነው፡ “እንሥራ” የሸክላ ሥራ ማኅበር፡፡
ማዕከሉ ዕድሜ ጠገቡ የኢትዮጵያ የሸክላ ሥራ ጥበብ በተሻለ ውበት እና ግርማ ሞገስ እውን የሚሆንበት የታሪክ ፋይዳ ያለው ቦታ ነው።
በማኅበር የተደራጁ የሸክላ ባለሞያ ሴቶች፣ ሁሉንም ዐይነት የሸክላ ውጤቶችን አስውበውና አሳምረው ያመርታሉ፡፡
ይሁንና ሥራው የተለያዩ ፈተናዎች ያሉበት እንደሆነ የሚገልፁት ባለሞያዎቹ፣ በአንዳንዶች ዘንድ የሚስተዋሉ የተዛቡ አመለካከቶች ከፈተናዎቹ መካከል እንደሆኑ ያስረዳሉ፡፡ ከአመለካከት ጋራ የተገናኙ ፈተናዎች፣ በአሁኑ ወቅት እየቀነሱ መኾናቸውንም ይገልጻሉ፡፡
የማዕከሉ አባላት ስለ ሥራው የሰጡንን ማብራሪያ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም