አዲሱ ዓመት ስድስተኛውን ቀን ብናገባድድም የበዐሉ ስሜት ገና አልጠፋምና በዚሁ ትኩስ ስሜት ከአድማጭ የተላከ አንድ ፅሁፍ ነው የምንተርክላችሁ፡፡ “እንቁጣጣሽ” በሚል ርዕስ የሾላው ማቴዎስ ታደሠ “የአንድ መንደር የበዐል ሁኔታ” ባሉት ግሩም መጣጥፋቸው የሾላን ልጆች ‹የአዲስ አበባውን ሾላ ሠፈር ማለታቸው ነው› የበዐል ትውስታ በትዝታ መነፅር ዓመታት ወደኋላ ተጉዘው የልጅነት ጊዜያቸውን ጨምረው ይቃኙበታል - “እንቁጣጣሽ” ሰሎሞን አባተ እንዲህ ተርኮታል፤ ያድምጡት፡፡
መታሰቢያ ለሾላ ልጆች