በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢንጂነር ስመኘው በቀለ መስቀል አደባባይ አካባቢ ሞተው ተገኙ


ኢንጂነር ስመኘው በቀለ
ኢንጂነር ስመኘው በቀለ

አስክሬኑም ተጨማሪ ምርመራ ሊደረግለት ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል መወሰዱ ተጠቁሟል፡፡

አስክሬኑም ተጨማሪ ምርመራ ሊደረግለት ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል መወሰዱ ተጠቁሟል፡፡

ጎንደር ልዩ ቦታው ማክሰኝት የተወለዱት ኢንጂነር ስመኘው፣ ህይወታቸው ላለፉት 32 ዓመታት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽንና በኢትዮጵያ ኃይል ሕዝብና መንግሥትን አገልግለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ኮተቤ ማሰልጠኛ ከ1978 እስከ 1991 ኢንስትራክተር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፣ ከ1991 እስከ 1992 ደግሞ በዋናው መሥሪያ ቤት የኢንጂነሪንግ ዲፖርትመንት ክፍል መሃንዲስ ሆነው ሰርተዋል፡፡

ኢንጅነር ስመኘው ሀገሪቱ የጀመረችውን የኃይል ልማቱ ዘርፍ በመቀላቀል ከ1992 1993 የጊቤ አንድ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ካውንተር ፓርት ኢንጅነር፣ ከ1997 እስከ 2002 የጊቤ ሁለት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አስተባባሪና እና ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም ከ2003 እስከ እስከ ሀምሌ 19፣ 2010 ድረስ ደግሞ የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ሆነው አገልግለዋል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG