በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤድስ በአፍሪካና በአሜሪካ “እየቀነሰ” በምሥራቅ አውሮፓና በእስያ “እያሻቀበ ነው”


 ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ
ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ

ዩናይትድ ስቴትስ ኤችአይቪን ለመቆጣጠር ባደረገችው ጥረት ግዙፍ ውጤት ማስመዝገቧ ተገልጿል።

ዩናይትድ ስቴትስ ኤችአይቪን ለመቆጣጠር ባደረገችው ጥረት ግዙፍ ውጤት ማስመዝገቧ ተገልጿል።

ፀረ-ኤችአይቪ/ኤድስ መድኃኒነቶችን ለሚያስፈልጋቸው በማዳረስ በኩልም የጎላ ሥራ መከናወኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፀረ-ኤድስ መርኃግብር - ዩ.ኤን.ኤድስ አስታውቋል።

የመንግሥታቱ ድርጅት ግብ በመጭዎቹ 12 ዓመታት ውስጥ ዓለምአቀፉን ወረርሽኝ ፍፃሜ ላይ ማድረስ ነው።

ይህ ሊደረስበት የሚችል ግብ ነው?

ኤድስ እንደ ሕይወት ፍፃሜ መርዶ ይታይ ከነበረባቸው የ1970ዎቹ ዓመታት መጨረሻ (በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር) አንስቶ ይህንን ወረርሽኝ ፍፃሜው ላይ ለማድረስ አንተኒ ፋውቺ እየጣሩ ናቸው።

እነሆ ወደ አርባ የሚጠጉ ዓመታት አለፉና ዶ/ር ፋውቺ በፅናትና በተስፋ የሚሉት አላቸው - ዛሬ ኤድስን እራሱን ፍፃሜው ላይ ለማድረስ አቅሙና መሣሪያውም እንዳላቸው ይናገራሉ።

“እጅግ የተዋጣላቸው መድኃኒቶች አሉን፤ እነዚያ መድኃኒቶች ታዲያ የሚወስዷቸውን ሰዎች ሕይወት ማዳን ብቻ ሳይሆን ቫይረሱ በደሙ ውስጥ የሚገኝነ ሰው የቫይረስ መጠን ሊታይ እስከማይችል ደረጃ ማውረድ መቻላቸው ያ ሰው ቫይረሱን ወደ ሌላ ሰው ማስተላለፍ እማይችልበት ሁኔታ ላይ ለማድረስ አብቅተዋል” ብለዋል ፋውቺ።

የዩናይትድ ስቴትሱ ብሄራዊ የጤና ኢንስቲትዩት ዳሬክተር አንተኒ ፋውቺ በመቀጠልም በመድኃኒቶች የሚሰጠው ሕክምና የቀለለ እንዲሆን መደረጉን ይናገራሉ።

በተጨማሪም ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ የሌለ ሰዎች እንዳይጋለጡ ማድረግ የሚችል ትሩቫዳ የሚባለው የመከላከያ መድኃኒት የቫይረሱን መዛመት በመግታት በኩል ቁልፍ ቦታ መያዙንም ፋውቺ አመልክተዋል።

በሌላ በኩል ግን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፀረ-ኤድስ መርኃግብር - ዩኤንኤድስ እንደሚለው ምንም እንኳን ሕክምና ከሚያስፈልገው ሰው ከግማሽ በላይ የሚሆነው በዓለም ዙሪያ አገልግሎቶችና መድጋኒት እያገኘ ቢሆንም ወደ 16 ሚሊየን የሚሆን ኤችአይቪ በደሙ ውስጥ የሚገኝ ሰው ሕክምናም መድኃኒትም እያገኘ አይደለም።

የባሰው አሳሳቢ ጉዳይ ግን ከእነዚህ ሰዎች የበዙቱ ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ መኖሩንም ስለማያውቁ በቀላሉ እያዛመቱት መቀጠላቸው አይቀርም። አንተኒ ፋውቺ እንደሚሉት ለዚህ መፍትሄው ክትባት ነው።

ታይላንድ ውስጥ እየተሞከረ ያለማ አንድ የኤችአይቪ ክትባት እስከ 31 ከመቶ በሆነ ደረጃ ስኬታማ መሆኑ እየተሰማ ነው።

ለኤችአይቪ የሚታሰበው ክትባት እስከ 99 ከመቶ ውጤታማ እንደሆኑት የኩፍኝን ክትባት እንደመሳሰሉ አይሁን እንጂ በሃምሣ እና በስድሣ ከመቶ ስኬታማነት እንኳ በሌሎቹ አካባቢዎች የተጨበጡትን የተራመዱ ግኝቶች እየተጠቀምን የኤድስን ወረርሽኝ ስፋትና አድማስ ዛሬ ከምናውቀው ሁኔታ መቀልበስና መፈፀም እንደሚቻል ፋውቺ እምነታቸውን ገልፀዋል።

ዋናው ቁም ነገር ግን፣ በብዙዎች እምነት፣ ብዙ ሰው ምርመራ ማድረግ፣ የጤና አገልግሎቶች ተጠቃሚ መሆን አለበት።

ባለፉት 17 ዓመታት ከሠሃራ በስተደቡብ ባለችው አፍሪካ የኤችአይቪ መተላለፍ መጠን በግማሽ መቀነሱን ዩኤንኤድስ አስታውቋል።

Red AIDS ribbon over globe
Red AIDS ribbon over globe

ይህ መጠን በምሥራቅ አውሮፓና በማዕከላዊ እስያ የሚያሳየው ቁጥር የተገላቢጦሹን ነው። ኤችአይቪ በከፍተኛ መጠን እያንሠራራና እየሰፋ ነው።

ዩኤንኤድስ በሚጠቅሳቸው በእነዚህ ሃገሮች ውስጥ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የኤችአይቪ ሥርጭት በስድሣ ከመቶ አሻቅቧል።

እንግዲህ የኤድስን ወረርሽኝ የመፈፀም ነገር - በጤና ኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር አንተኒ ፋውቺና በመንግሥታቱ ድርጅት መርኃግብር - ዩኤንኤድስ እምነት - በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እጅ ውስጥ ያለ ብያኔ ነው።

ያንን ግብ ለመጨበጥ ምን ያህል ገንዘብና ጉልበት ይመድብና ያፈስስ ይሆን? ለኤድስ ፍፃሜ የቀሩት 12 ዓመታት ናቸው - የዘላቂ ልማት ግቦች ግብ ቁጥር ሦስት!

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ኤድስ በአፍሪካና በአሜሪካ “እየቀነሰ” በምሥራቅ አውሮፓና በእስያ “እያሻቀበ ነው”
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:09 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG