ኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱት ፋኖና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች፣ በምክክር ሂደቱ እንዲሳተፉ የማድረግ ፍላጎት እንዳለው፤ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዛሬ አስታወቀ።
አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡት፣ ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ፣ የታጣቂ ቡድኖቹ የደኅንነት ኹኔታ ተጠብቆ ከኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች ጋራ እንዲወያዩ ለማድረግ ኮሚሽኑ ዝግጁ መኾኑን ተናግረዋል። ኮሚሽኑ የተቋቋመበት ዐዋጅም ይህንን ሂደት እንደሚፈቅድላቸው ዋና ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
በፀጥታ ችግር ምክኒያት በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ውይይት ማካሄድ እንዳልቻለ የገለፀው ኪሚሽኑ፤ ዛሬ ግን ተሳክቶለት በሻሽመኔ ከተማ ማካሄዱን አስታውቋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡
መድረክ / ፎረም