አዲስ አበባ —
የፊታችን ሰኞ ለሚካሄደው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምርጫ የሚሳተፉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምረጡኝ ዘመቻ በዛሬው ዕለት የተጠናቀቀ መሆኑን የምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡ የምርጫ ቦርድ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች አማካሪ ሶልያና ሽመልስ ቀሪዎቹ አራት ቀናት የምርጫ ቅስቅሳዎች የማይኬዱባቸው፣ ማኅበረሰቡ ስለ ድምፅ አሰጣጥ ብቻ መረጃ የሚያገኝበትና ማንን መምረጥ እንዳለበት ለማሰብ የጽሞና ወይም የጸጥታ ጊዜ የሚያገኝበት መሆኑን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎችና ደጋፊዎቻቸው በተለይ ትናንትና ዛሬ የመጨረሻ ቅሰቀሳቸውን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያካሄዱ ሲሆን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶ/ር ራሄል ባፌ፣ የምርጫው ሂደት ለዚህ ደረጃ መብቃቱን ገልጸው፣ ተስፋና ሥጋቱ ግን ከምርጫውም በኋላ የሚቀጥል በመሆኑ ቀሪ ሥራዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡