በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቨርጂኒያ የጅምላ ክትባትን ለኢትዮጵያውያን ያመቻቸው ቤተክርስቲያን


አማኑኤል የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤክርስቲያን
አማኑኤል የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤክርስቲያን

ሰሞኑን በዋሽንግተን አካባቢ ለሚገኙ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ አባላት የጅምላ የክትባት መስጫ ሆነው ከአገለገሉት የመጀመሪያው ተቋም በቨርጂኒያ ስፕሪንግ ፊልድ ፍራንኮኒያ ላይ የሚገኘው የአማኑኤል የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤክርስቲያን መሆኑን የቤተክስርቲያኒቱ አስተዳዳሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡

በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ አሜሪካውያንንም ጨምሮ የሌሎች አገር ዜጎችና የተለያዩ እምነት ተከታዮችም ክትባቱን በቦታው ተገኝተው መውሰዳቸውንም ገልጸዋል፡፡

አሁንም ሁለተኛውን ዙር ክትባት መሰጠት የተጀመረ ሲሆን በመጭው አርብ ኤፕሪል 23/2021 ቁጥራቸው ከ2ሺ በላይ ለሚሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና አሜሪካውያን ለመስጠት እየተዘጋጁ መሆኑን ኃላፊዎቹ አስታውቀዋል፡፡

ቤተክርስቲያኑ የሚሰጣቸው ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶችን በማካተት የቤተ ክርስቲያኑ ሲኒየር ፓስተር አበራ ተሰማ እና የቤተክርስቲያኑ ሽማግሌዎች ሰብሳቢን አቶ አማረ መሳይን አነጋግረናቸዋል፡፡

ቀሪውን ከተያይዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

በቨርጂኒያ የጅምላ ክትባትን ለማህበረሰቡ ያመቻቸው ቤተክርስቲያን
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:06 0:00


XS
SM
MD
LG