በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢላን መስክ ለመራጮች በሚሰጡት የሚሊዮን ዶላር ስጦታ ጉዳይ ለቀረበባቸው ክስ ችሎት ሳይገኙ ቀሩ


የተስላ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢላን መስክ
የተስላ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢላን መስክ

መስክ የፊታችን ጥቅምት 26 ከሚካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አስቀድሞ ለመራጮች የሚሰጡትን 1 ሚሊዮን ዶላር ስጦታ አስመልክቶ የቀረበባቸውን ክስ ከሚሰማው የፔንስልቬንያ ችሎት መክፈቻ ነው ሳይገኙ የቀሩት። ይህም ችሎት በመናቅ የመከሰስ አደጋን ሊደቅን መቻሉ ተገልጧል።

የሪፐብሊካኑን እጩ ዶናልድ ትራምፕን የሚደግፉት ቢሊየነር ኢላን መስክ፤ በትረምፕ እና በዲሞክራቷ ዕጩ ካማላ ሃሪስ መካከል ብርቱ ፉክክር ከሚታይበት እና አንድ ሳምንት የማይሞላ ጊዜ ከቀረው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አስቀድሞ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በስጦታ መልክ ለመራጮች የሚሰጡበትን ድርጊታቸውን እንዲገቱ’ የፊላዴልፊያ ወረዳ አቃቤ ሕግ ላሪ ክራስነር ያቀረቡትን ክስ ከሚያዩት ዳኛ ፊት ነበር እንዲቀርቡ የታዘዙት፡፡ ይሁን እንጂ መስክ ችሎቱ ዛሬ ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ ሲጀምር እንደታዘዙት በፍርድ ቤቱ አልተገኙም።

ትልቁ የአለማችን ባለጸጋ ዳኛው አንጌሊዮ ፎግሊየታ ችሎት በመናቅ ተጠያቂ ካደረጓቸው መስክ ቅጣት ሊጠብቃቸው ይችላል።

በሌላ በኩል መስክ ጉዳዩ ወደ ፌዴራል ፍርድ ቤት እንዲዛወርላቸው ጠይቀዋል። ይህም እገዳው እንዲዘገይ እና ለመራጮች ስጦታ በመስጠቱ እንዲቀጥሉ የሚያስችል እድል የሚፈጥር ዘዴ ነው ተብሏል።

ለዋና አቃቤ ሕግነት በተወዳደሩበት ወቅት ለዲሞክራቶች ያላቸውን ድጋፍ ያንጸባረቁት ክራስነር፤ የቴስላውን ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስክን እና ለፖለቲካ ድጋፍ ያቋቋሙትን ‘አሜሪካ ፓክ’ የተባለ ቡድናቸውን በመራጮች ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር በታለመ ሕገ-ወጥ ሥራ ነው የወነጀሉት።

መስክ የአንድ ሚልዮን ዶላሩን ቼክ የነጻ ንግግር እና የጦር መሳሪያ ባለቤትነት መብቶችን ለመደገፍ ቃል ከገቡ ሰዎች ውስጥ የሎተሪ እጣ ለደረሳቸው ሲሰጡ መቆታቸው ነው የተዘገበው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG